እንኳን ወደ አዲሱ የደብራችን ድረ ገጽ በደህና መጡ!

የለንደን ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን፣ ሰሜን ምዕራብ አውሮጳ ሀገረ ስብከት ሥር የምትገኝ አጥቢያ ስትሆን በሰሜኑ የለንደን ክፍል ላለፉት ፲ ዓመታት አገልግሎት በመስጠት ላይ የምትገኝ አጥቢያ ነች።

ልዑል እግዚአብሔር ቢፈቅድ፣ በዚህ ድረ ገጽ

  • ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን
  • ወቅታዊ መረጃዎችን እና
  • አባልነትን መከታተያ ማኅደር /membership database/

እና የመሳሰሉትን ለማቅረብ አቅደናል። ገጾቹን ከማንበብ በተጨማሪ ይጠቅማል የሚሉትን በማካፈል፣ ይጎድላል የሚሉት ካለ በመጠየቅ እንዲሳተፉ በትህትና እንጋብዛለን።

መልካም ቆይታ

የአብርሃሙ ሥላሴ

በሊቀ ጉባኤ ጥበበ ሥላሴ አሰፋ

ሐምሌ 7 ቀን እግዚአብሔር በአንድነት፣ ሥላሴ በሦስትነት ለአብርሃም በቤቱ የተገለፁበት፣ በእንግድነት ተገኝተው ቤቱን የባረኩለት፣ በበጎ ህሊናው በትሁት ስብዕናው ያቀረበላቸውን ማዕድ የባረኩለትና ለሣራም ማህፀኗን ባርከው በስተእርጅና ይስሐቅን እንደምትወልድ ያበሰሩት ዕለት ነው።

አንድነትን ሦስትነትን የምንማርበት ትምህርት ቢኖር ዋነኛው እግዚአብሔር በአብርሃም ቤት የተገለፀውን መገለፅ መመልከትና መመርመር በቂ ነው። ታሪኩን በሙሉ በቅዱስ መጽሐፍ እናገኘዋለን ኦሪ. ዘፍ 18-1-33 

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም፣ በግብር፣ በአካል ሦስት፤ በባህርይ፣ በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በፈቃድ አንድ ናቸው። ለዘመናቸው በዚህ ጊዜ ተገኙ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አንልም ፊተኛና ኋለኛ፣ መጀመርያና መጨረሻ፣ አልፋና ኦሜጋ ናቸው። ራዕ 22፥13

ሕንጻ

በልዑል እግዚአብሔር ቸርነት ደብራችን ከተመሠረተች ጀምሮ ላለፉት አሥር አመታት አገልግሎት በመስጠት ላይ ትገኛለች። የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ሁሌም በፈተና ውስጥ ነው። በተለይ በውጭው አለም ለሚገኙ አጥቢያዎች ሁሉ ማለት ይቻላል አገልግሎታቸውን የሚሰጡበት በቋሚነት የሚገለገሉበት ሕንጻ አለመኖር አንዱ ትልቁ ፈተና ነው።

ከደብሩ ምሥረታ ጀምሮ በኪራይ ስንገለገልበት የቆየው "ተፍነል ፓርክ" አካባቢ የሚገኘው የቅ. ጊዮርጊስ የአንገሊካን ቤተ ክርስቲያን እ.ኤ.አ. 2013 ዓ.ም. ሕንጻውን ለእድሳት እንደሚፈልጉት በመግለጽ ሌላ ቦታ እንድንፈልግ ጠየቁን። በልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ፣ በወቅቱ በነበሩ ካህናት እና ምእመናን ፍለጋ እና በሰ/ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት ትብብር ሌላ ሕንጻ በኪራይ ለማግኘት በቃን። በአሁኑ ወቅት እየተገለገልንበት ያለውን ይኼንኑ የቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ደግሞ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለቅቀን እንድንወጣ ተጠይቀናል።

የተጠቃሚ መግቢያ