በስመ አብ፣ ወወልድ፣ ወመንፈስ ቅዱስ፣ አሐዱ አምላክ፣ አሜን

እንኳን ለጌታቸን እና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ልደት በሰላም አደረሳችሁ!

"ሕዝቤ ሆይ፥ ና ወደ ቤትህም ግባ፥ ደጅህን በኋላህ ዝጋ ቍጣ እስኪያልፍ ድረስ ጥቂት ጊዜ ተሸሸግ።" ት. ኢሳ. 26፥20

ጌታችን "የቄሣርን ለቄሣር" ብሎ እንዳስተማረን፣ በዚህ ምድር እንደሚለላሱ ሰዎች ሕገ እግዚአብሔርንም፣ ወደኃጢአት ከሚመራው በቀር ሕገ ሰብእንም አክብረን መጓዝ ይጠበቅብናል። በመሆኑም በጊዜው በሥራ ያሉትን የመንግስት ሕጎችና ደንቦች መሠረት በማድረ

  1. አስቀድመው በደብሩ ሰ/ጉባኤ ጽ/ቤት ተመዝግበው ወረፋ ሲጠባበቁ የነበሩ ክርስትና ለሚያስነሱ ቤተሰቦች (በተመደቡብበት ዕለት ብቻ)

  2. የንስሐ አባታቸውን አነጋግረው ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ለተዘጋጁ፣ ስማቸው ለጽ/ቤቱ ለተላለፈ ምእመናን

ከዚህ ውጪ ቦታው እስከፈቀደ ድረስ ማንኛውም ምእመን ገብቶ መገልገል የሚችል ሲሆን የተመደበው ቁጥር ሲሞላ ግን ውጪ ተራ መጠበቅ ግድ መሆኑን ከወዲሁ ማስታወቅ እንወዳለን።

ብዙ አገልግሎት የሚጠብቁ ምእመናን መኖራቸውን በመገንዘብ የደብሩ ካህናት ክመደበኛ የእሑድ እና የወር በአላት በተጨማሪ ዘወትር ቅዳሜም የቅዳሴ አገልግሎት መስጠት የጀመሩ በመሆኑ ሁላችሁም በትእግስት እና በከርስቲያናዊ ሥነ ምግባር በመታዘዝ የአገልግሎቱ ተካፋዮች እንድትሆኑ በትህትና እናሳስባለን። ከዚህ ውጪ ደግሞ ቦታው በሚፈቅደው መጠን/ብዛት/ በቁጥር ውሱን የሆኑ ምእመናን በአመጣጣቸው ቅደም ተከተል ገብተው መገልገል ይችላሉ። የሠርክ መርሃ ግብሩ ላይ እስከ አሁን እንደቅዳሴው ሰው ስለማይበዛበት ለመሳለም ብቻ ለሚመጡ ምእመናን ሠርክ ላይ መምጣቱ የተሻለ አማራጭ ሊሆን ይችላል።

አሁንም አገልግሎቶቻችንን በYouTube ቻነላችን ላይ ማስተላለፉን እንቀጥላለን።

ልዑል እግዚአብሔር ቁጣውን በትዕግስት፣ መዓቱን በምኅረት እንዲመልስልን፣ ለአለም ሁሉ ይቅርታውን እንዲልክ፣ በልዩ ልዩ ፈተና ውስጥ ያሉትን ወገኖችን በቸርነቱ እንዲታደጋቸው እንጸልይ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

In the name of The Father, and of The Son, and of The Holy Spirit, Amen

"Come, my people, enter your chambers, And shut your doors behind you; Hide yourself, as it were, for a little moment, Until the indignation is past." Isiah 26:20

COVID-19 Update

Following the changed government guidelines from 4 July, our church has started giving the following limited service.

The following people will have priority to enter the church.

  1. Those who have been on the waiting list for baptism, and have been assigned a date the parish office.

  2. Those who, after consulting their fathers of confession, have been booked to take part in Holy Communion.

Additionally, a few more people will be allowed to come in - up to the limit that still allows for social distancing. Please, note that you might have to queue outside once the capacity has been reached.

Our clergies are holding additional Saturday services to accommodate those on the waiting list, hence we kindly ask you to wait patiently. Please, note that the daily evening prayers are not as busy and may be more suitable for those who are not planning to take part in sacramental services. In the meantime, we continue to stream our services live on our YouTube channel.

Let us all pray from God's mercy to save the whole world. Let us also remember everyone who are facing different types of challenges at this testing time.

Thank you for your understanding and may God bless you.