የሰ/መ/አ/ጉባኤ ምርጫ
Trustees Election

የለንደን ደ/ገነት ቅ/ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ምርጫ ለማካሄድ አስመራጭ ኮሚቴ ተሰይሞ ሥራ መጀመሩ የሚታወቅ ነው።

የዘንድሮውን ምርጫ የምናስተናግደው ያለፈው ምርጫ ላይ የተጠቀምንበትን ኦንላይን ሲስተም በመጠቀም ይሆናል። ሲስተሙ ለምርጫ የተዘጋጀ በመሆኑ፣ ለመራጮች ምስጢራዊነትን ስለሚጠብቅ እና የድምጽ ቆጠራውን የተቀላጠፈ ስለሚያደርገው የተሻለ አማራጭ ሆኖ ተገኝቷል።  

ለምርጫው የዕጩዎችን ጥቆማ እሑድ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. /07 July 2024/ ከቅዳሴ በኋላ በቤተ ክርስቲያናችን የሚካሄድ ሲሆን፣ ምርጫው ደግሞ እሑድ ሐምሌ 14 ቀን 2016 ዓ.ም. /21 July 2024/ ይካሄዳል።

ከደብሩ ጽ/ቤት ባገኘነው መረጃ መሠረት በደብሩ የሰበካ ጉባዔ ለተመዘገቡ አባላት በኢሜይል እና/ወይም በስልክ መልእክት/Text Message/ የምናሳውቅ ሲሆን፣ በአድራሻ ለውጥ፣ በአድራሻ አለመሟላትም ይሁን በሌሎች ምክንያቶች ይህ መልእክት አስከ እሑድ ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም. /07 July 2024/ ያልደረሳችሁ አባላት በአስቸይህንን ቅጽ በመሙላት ወይም ከታች ወደተጠቀሰው ኢሜይል በመጻፍ መራጭ ኮሚቴውን እንድታሳውቁ እናሳስባለን። በደብሩ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ባልና ሚስት የየራሳቸው ድምጽ የሚያገኙ ሲሆን ይህ መልእክት ለእርስዎ ደርሶዎት ለባለቤትዎ ግን ያልደረሰ ከሆነ ባለቤትዎ ቅጹን እንዲሞሉና እንዲያሳውቁን ያበረታቱልን ዘንድ አደራ እንላለን።

በመጨረሻም በጥቆማው አና በምርጫው ላይ በመገኘት የበኩልዎን መንፈሳዊ ግዴታ አንዲወጡ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም አደራ አያልን፣ ልዑል አግዚአብሔር ቤቱን በቅንነትና በትጋት የሚያገለግሉትን አንዲያዘጋጅ፣ ለእኛም ሥራችንን የተቃና እንዲያደርግልን በጸሎት አንዲያቡን በትህትና አንጠይቃለን።

እግዚአብሔር ይስጥልን።

አስመራጭ ኮሚቴው (election2024@dght.uk)

ዲ/ን አዳም አወት፣ ዲ/ን ሚሊዮን አጀበ፣ አቶ ኢሳይያስ መኩሪያ፣ አቶ ሄኖክ ብርሃኔ፣ ወ/ሮ ማርታ ዘለቀ እና አቶ በረከት ገነቱ

---------------------------

Our parish, London D.G. Holy Trinity, is in the process of electing new Parish Council Administration Committee members (Trustees).

In the previous Trustee election we had, an online system was used. The Election Committee has agreed to use the same system this year, as it is tailor-made for this purpose, simplifies vote counting, and keeps the votes anonymous.

The Committee will accept nominations for Trusteeship from members on Sunday 07 July 2024, while the election will be held on Sunday 21 July 2024.

We will be sending registered members an individual message using the contact details held on file. However, we urge any member who has not received a copy of that message by Sunday 30 June 2024 to contact the Election Committee either by completing this short form or by using the email address below.

As per the constitution of our church, couples (husband and wife) get one vote each. If you have received the election notice, but your spouse has not, please encourage your spouse to kindly let us know so that we can add them.

Finally, we kindly ask that you fulfil your spiritual duty by taking part in both the nomination and election, as well as remembering us in your prayers.

God bless,

The Election Committee (election2024@dght.uk)

(Dn Adam A., Dn Million A., Mr Esayas Mekuria, Mr Henok Berhane, Ms Martha Zeleke & Mr Bereket Genetu)